እንደ መንደርደርያ ይሀ መጽሃፍ በዋሽንግተን ዲሲ – ሳንኮፋ ቢሮ ውስጥ ሲመረቅ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝቼ ነበር። መገኘት ብቻ ሳይሆን በዝግጅቱ ላይ ግራ ያጋቡኝን ጥያቄዎች ለመጽሃፉ ደራሲ አቅርቤለት ነበር። የኔ ግርታ ምናልባትም የብዙዎቻችሁ ጥያቄ ሊሆን ስለሚችል እዚህ ላይ እንደገና ማንሳቱን መረጥኩ። የመጀመርያው ጥያቄ “ይህ ታሪክ 30 አመታት አለፈው። ታዲያ አንድ ትውልድ ካለፈ በኋላ አሁን ይፋ መሆኑ [...]
↧