በቅርቡ ለንባብ የበቃው “ድርጅታዊ ምዝበራ” የተሰኘው መጽሃፍ ደራሲ ዶክተር ኣክሎግ ቢራራ ጎንደር ተማሪ በነበሩበት ወቅት በኣንድ ነገር ተመስጠው ነበር። ይህ ምናባቸውን የገዛው ነገር በጎንደር ውስጥ እድሜው የትየለሌ የሆነ የኣንድ የዋርካ ዛፍ ተፈጥሮ ነበር። ይህን ዋርካ ባዩት ቁጥር ምናባቸው ተዛምዶን ይፈጥራል። ግዙፉ ዋርካ ዙሪያውን ያሉትን ቅርንጫፎችና ቅጠሎች ይዞ ዝንት ዓለም ይኖራል። ከምድሪቱ የሚያገኘውን ኣስፈላጊ ነገር እያመላለሰ [...]
↧